ይህ መጽሐፍ፣ በወቅታዊ ንጥል ጥናቶች ላይ ተመሥርቶ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ ልምዶችንና ዕውቀቶችን አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ስለ አገራዊ ምክክር በየጊዜው እያደገ ለመጣው ውይይት አስተዋጽኦ ማድረግን ያለመ ነው። እንዲህ በማድረግም፣ ስልታዊ ማብራሪያዎችን እያቀረበ ተግባራዊ ምክሮችን ይሰጣል። ስለዚህም መጽሐፉ (አገራዊና ዓለም አቀፋዊ) የግጭት አፈታት ባለድርሻዎችንና ባለሙያዎችን በመደገፍ ለየራሳቸው አውዶች ተገቢ የሆኑ አወቃቀሮችን በመመሥረት ፈተናዎቻቸውን እንዲቋቋሙ ያግዛል። መጽሐፉ፣ ከቀላል አቀራረቡም ባለፈ፣ የአገራዊ ምክክር ሂደትን በሚመለከት ከምሁራንና ከባለሙያዎች የተገኙ ዕውቀቶችንና ልምዶችን ቅኝት ያቀርባል። የመጽሐፉ ዓላማ ሁለት እጥፍ ነው፡- (1) ስለ አገራዊ ምክክር መድረኮች አወቃቀር ትንተናዊ ማዕቀፍ መስጠት (2) በነዚህ ሂደቶች ለሚሰማሩ ባለሙያዎች ተግባራዊ መመሪያ ሆኖ ማገልገል ነው።
ስለዚህም ይህ መጽሐፍ አገራዊ ምክክሮችን ሁሉን አቀፍ በሆነ መልክ ለማዋቀር፣ ለመተግበርና ለመደገፍ የተ ግባር- ተኮር መመሪያ ይሰጣል።
Case Studies Constitution Building Constitutionalism National Dialogue Negotiations Peace Building Political Dialogue Reconciliation